የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር በመተባበር ከሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር በሰላም ግንባታ ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን ትውልድን የማነጽና ሀገርን የመገንባት ጉዳይ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው።
በመሆኑም ለሀገር ዘላቂ ሰላም፣ መቻቻል እና አብሮነት መጠናከር በአርዓያነት አበክረው ሊሰሩ እንደሚገባ አመላክተዋል።
የሰላም ሚኒስትሩ እንደገለጹት በመገናኛ ብዙሃኖቹ የሚተላለፉ መልዕክቶች የራስን ብቻ ሳይሆን ሌላው እንዴት ይመለከተዋል የሚለውን ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን ማየት ይገባል።
የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዮናታን ተስፋዬ አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ የሃይማኖት መገናኛ ብዙሀን ህጋዊ ሰውነት እንዲኖራቸው ማስቻሉን ተናግረዋል።
መገናኛ ብዙሀን የሚያስተላልፏቸው መልእክቶች ሰላምን በሚያመጣ እና አብሮነትን በሚያጠናክር መንገድ መሆን እንዳለበትም ተናግረዋል።
በመድረኩ በተቀመጡ አቅጣጫዎች መሰረትም በይዘት ስራዎቻቸው ለሰላም ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ