February 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አርሰናል ከካራባኦ ዋንጫ ተሰናበተ

ማሻ፣ ጥር 29፣ 2017 (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) በእንግሊዝ የካራባኦ ዋንጫ ውድድር አርሰናል በደርሶ መልስ ጨዋታ ተሸንፎ ከውድድሩ ተሰናብቷል።

በትላንትናው ዕለት በተደረገ የእንግሊዝ ካርስባኦ ዋንጫ ጨዋታ አርሰናልን በሜዳው ያስተናገደው ኒውካስትል ዩናይትድ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለፍፃሜ ጨዋታው ማለፉን አረጋግጧል።

በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ወደ ኢሚሬትስ ተጉዞ 2 ለ 0 አሸንፎ የተመለሰው ኒውካስትል በሁለተኛው ጨዋታ ላይም በተመሳሳይ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

በተያያዘ ዜና በዛሬው እለት በእንግሊዝ ካራባኦ ዋንጫ ወደ ፍፃሜ ለማለፍ የሚደረግ አንድ ተጠባቂ ጨዋታ 5፡00 ላይ ይካሄዳል።

በዚህ ጨዋታ በውድድር ዓመቱ ደካማ እንቅስቃሴ እያሳየ የሚገኘው ቶተንሀም አስደናቂ የውድድር ዓመት በማሳለፍ ላይ የሚገኙትን ሊቨርፑልን ይገጥማሉ።

በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት የተሸነፈው ሊቨርፑል በመልሱ ጨዋታ ውጤቱን ሊቀለብስ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

ኤፍ ኤም ሲ

በዚህ ጨዋታ ማሸነፍ የሚችል ቡድን በፍፃሜ ጨዋታ አርሰናልን አሸንፎ ያለፈውን ኒውካስትል ዩናይትድን ይገጥማል።