February 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የክልሉ ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ/ም የፈተና ዝግጅት አስተዳደር አፈፃፀም ግምገማ እና የ2017 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የተፈታኝ ተማሪዎች በበየነ መረብ ምዝገባ ላይ ስልጠና እየሰጠ ነው።

በስልጠናው መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የቢሮ ምክትል ኃላፊና የመማር ማስተማርና ምዜና ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ደስታ ገነመ (ዶ/ር) የ2016 ዓ/ም አፈፃፀም በመገምገም ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ጥንካረውን ለማስቀጠልና ጉድለት በመለየት እንደ ግብዓት በመውሰድ በቀጣይ በማረም የፈተና አስተዳደር ስርዓትን ለማዘመን ያለመ እንደሆነ አንስተዋል ።

አክለውም ክልሉ አዲስ ቢሆንም ለ3ኛ ዙር

የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የፈተና አስተዳደር ስርዓትን ማዘመን ወሳኝ በመሆኑ የተማር ከምዝገባ ሂደት፣ የፈተና አሰጣጥ፣ እርማትና ውጤት ማሳወቂያ ድረስ ያለውን በበየነ መረብ(Online) ለማስከድ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል ።

ፈተናውን በበየነ መረብ (Online) መስጠት ብዙ ጠቀሜታ መኖሩን ያወሱት ዶ/ር ደስታ ኩረጃን በማስቀረት ብቁ ተማሪዎችን ወደ ቀጣይ ክፍል ለማሳለፍና ፎርድ መረጃን ለመከላከል እንዲሁም ተማሪውን ከቴክኖሎጂ ጋር በማላመድ ብቁና ተወዳዳሪ ለማድረግ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

በመሆኑም የሀገር በቀል ቴክኖሎጂ ሶፍትዌር ከሆነው ከቀለም ሜዳ በመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች የክህሎት ስልጠና እንደሚሰጥና ይህም አምና የታዩ ጉድለቶችን ለመፍታትና አዳዲስ በዘርፉ የተቀላቀሉ ባለሙያዎችን ለማብቃት እንደሚረዳ ም/ቢሮ ኃላፊው አክሏል።

በ2016 ዓ/ም በ1118 የፈተና ጣቢያ 48,000 ተማሪዎች ከተፈተኑት 19,500 ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል አፈፃፀም 42% መሆኑን ያወሱት ም/ኃላፊው ባለፈው ዓመት ያጋጠሙ ፎቶውን በአግባቡ ከመለጠፍ፣ ፆታና ስምን በአግባቡ ከማስገባት አንጻር የተከሰቱ ጥቃቅን ችግሮችን ከወዲሁ ለመፍታት ተሳታፊዎቹ የተግባር ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ በአጽንኦት አሳስበዋል ።

የ2016 ዓ/ም የ8ኛ እና 12 ክፍለ ክልላዊና አገራዊ የፈተና አፈፃፀም ሪፖርት ለውይይት ለመነሻነት የፈተና ዝግጅት አስተዳደርና ትምርህት ምዜና ጥራት ዳይሬክተር በአቶ ሲሳይ ኃ/ሚካኤል ለተሳታፊዎች እየቀረበ ይገኛል ።

በስልጠና መድረኩ የክልሉ ቢሮ የዘርፍ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊዎች፣ የዞንና ወረዳ የፈተና አስተዳደርና ዝግጅት ክፍልና የICT ባለሙያዎችና ሌሎች የባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

#south west communication