የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2017 ግማሽ ዓመት የመንግሥትና የፓርቲ የእቅድ አፈጻጸም በቦንጋ ከተማ እየተገመገመ ይገኛል።
በመድረኩ የአስፈጻሚ አካላት እና የፓርቲ ተግባር አፈጻጸም በጋራ እየተገመገመ የሚገኝ ሲሆን ይህም አሰራር ተግባራዊ መድረጉ በተግባር አፈጻጸም ወቅት የሚገጥሙ ችግሮችን በቅንጅት ለመፍታት እንደሚረዳ ተገልጿል።
በዚህ የተግባር አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በክልሉ አዳጊ ልማት ለማምጣት ያለመና ከአስር ዓመቱ የልማት እቅድ የተቀዳ የመካከለኛ ጊዜ የልማት እቅድ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።
በበጀት ዓመቱ ግማሽ አመት የተከናወኑ ጠንካራ ተግባራትን በማስቀመጥና ያጋጠሙ ችግሮችን ፈጥኖ በማረም በሚቀሩ ጊዜያት አፈጻጸሙን ከእቅዱ አኳያ ማሳካት እንደሚባ ነው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የገለጹት።
የክልሉን ሁለንተናዊ የልማት አቅም መሠረት አድርጎ የተዘጋጀውና በቀጣይ ሶስት ዓመታት የሚተገበረው እቅዱ፥ በየደረጃው ወይይት ተደርጎ የየአካባቢውን ተጨባጭ የልማት አቅሞች አቀናጅተው ወደ ልማት ለመግባት የሚረዳ መሆኑን ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የገለጹት።
ርዕሰ መስተዳድሩ አክለው መድረኩ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛው ጉባኤው የተቀመጡ አቅጣጫዎችን መሠረት በማድረግ በየደረጃው ያለው አመራር፥ የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማሳደግ የጋራ ግንዛቤ የሚጨበጥበት እንደሆነም ጨምረው ገልጸዋል።
የፓርቲና አስፈፃሚ ተቋማት የተግባር አፈጻጸም በጋራ መገምገሙ በተግባር አፈጻጸም ወቅት በሚያጋጥሙ ችግሮች ላይ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ፥ የጋራ የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ የጎላ ፋይዳ እንዳለው የገለጹት የክልሉ ዋና የመንግሥት ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን ይህ ተግባር በየደረጃው ባሉት መዋቅሮችም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።
የአመራር የአስተሳሰብ አንድነትን በማጠናከር የተግባር ውጤታማነትን ማረጋገጥ ይገባል ያሉት አቶ ፍቅሬ በየአካባቢው ያሉ የልማት ፀጋዎችን በመለየት ወደ ተጨባጭ ልማት መቀየር ከአመራሩ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑንም ተናግረዋል።
በመድረኩ የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን በቀል ዝርዝር የአስፈጻሚ ተቋማትን የተግባር አፈጻጸም ሪፖርት እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ የፓርቲ ተግባራት አፈጻጸምም እንደሚቀርብ ተገልጿል።
በመድረኩ የክልል ማዕከል አመራሮች፣የዞን እና የከተማ አስተዳደር የፊት አመራሮች እየተሳተፉ ነዉ።
#SW communication
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።