ትራምፕ በኋይትሀውስ በሰጡት መግለጫ ዋሽንግተን በድጋፍ መልክ ካፈሰሰችው 300ቢሊየን ዶላር ጋር የሚስተካከል ክፍያ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በምታደርገው ጦርነት ላደረገችላት የፋይናንስ ድጋፍ በክፍያ መልክ ውድ የመሬት ማዕድናትን እንድትሰጣት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።
ትራምፕ በኋይትሀውስ በሰጡት መግለጫ ዋሽንግተን በድጋፍ መልክ ካፈሰሰችው 300ቢሊየን ዶላር ጋር የሚስተካከል ክፍያ እንደሚፈልጉና ለዚህም ዩክሬን ፈቃደኛ ነች ብለዋል።
“ዩክሬን ውድ ዋጋ ያላቸው ብርቅ የመሬት ማዕድን እንዳላት ነግረናታል” ብለዋል ትራምፕ። “ዩክሬን የሰጠናትን ድጋፍ በውድ ማዕድናት እንድትከፍለን እየተወያየን ነው።”
ትራምፕ ስለየትኞቹ ውድ ማዕድናት እያወሩ እንደሆነ ገልጽ አላደረጉም። ውደ ማዕድን የሚባለው ኃይልን ወደ እንቅስቃሴ በመቀየር ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች፣ ለሞባይ ስልክና ለሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች የሚያገለግሉ 17 ማዕድናትን ያካተተ ቡድን ነው።
እስካሁን እነዚህን ብረቶች የሚተካ ማዕድን የለም።
እንደ አሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ ከሆነ ኒኬልንና ሊቲየምን ጨምሮ 50 ማዕድናት ለአሜሪካ ኢኮኖሚና ብሔራዊ መከላከያ እጅግ ወሳኝ ተብለው ተለይተዋል።
ዩክሬን የዩራኒየም፣ ሊቲየምና የቲታኒየም ከፍተኛ ክምችት ያላት ቢሆንም በመጠን በአለም ቀዳሚ አምስት ውስጥ የለችበትም። አሜሪካ እነዚህን ጨምሮ ሌሎች ወሳኝ ማዕድናት ክምችት ያላት ሀገር ነች።
አሜሪካ በዝቅተኛ አቅም የሚንቀሳበስ አንድ የውድ ማዕድን ማውጫ ብቻ ያላት ሲሆን ቻይና በአንጻሩ ውድ ማዕድናትና ወሳኝ ማዕድናትን በምረት ከአለም ቀዳሚ ነች።
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።