April 4, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ስኬት በጠንካራ ሥራ ብቻ እንደሚገኝ የሚያስተምረው የክርስቲያኖ ሮናልዶ ሕይወት

ማዴራ ከምትባል አንዲት ትንሽ መንደር ተነስቶ ዓለምን ያስጨበጨበ ስኬት ላይ የደረሰው ክርስቲያኖ ሮናልዶ 40 ዓመቱን ደፍኗል። በጣም አስገራሚው ነገር ግን ዛሬም በ20ዎቹ ዕድሜ እንደሚገኙት ተጨዋቾች ነው ኳስን የሚጫወተው። በእግር ኳስ ሕይወቱ ያለገኘው ሽልማት የለም፤ ከዓለም ዋንጫ በስተቀር ያላሳካው ዋንጫም የለም።

ይህን ሁሉ ያሳካው ሮናልዶ ግን እዚህ የደረሰው አልጋ በአልጋ በሆነ ጉዞ አይደለም። የተወለደው እ.አ.አ ፌብሩዋሪ 5 ቀን 1985 በፖርቱጋሏ ማዴራ በምትገኝ ፉንቻል በምትባል መንደር ከድሃ ቤተሰብ ነው።

እናቱ ምግብ አብሳይ ሆነው ይሠሩ የነበረ ሲሆን፣ አባቱ ደግሞ በአካባቢው በሚገኝ ክበብ ውስጥ ይሠሩ ነበር። በኋላም ልጃቸው ትልቅ እንዲሆንላቸው ሲንከባከቡት የነበሩት አባቱ እሱ ገና ለጋ ሳለ ሞቱ። እናም ሁሉም ኃላፊነት በእናቱ ላይ ወደቀ። እሱም እናቱን ለመርዳት ጎዳና እስከማጽዳት የደረሰ ሥራ መሥራት ጀመረ።

ጎን ለጎንም የቀጣይ ስኬቱ መዳረሻ የሆነውን እግር ኳስን መጫወቱን ቀጠለ። በ12 ዓመቱም የስፖርቲንግ ክለብ አካዳሚ ውስጥ የመግባት ዕደሉን አገኘ። ከተወለደበት አካባቢ ለቅቆ ክለቡ ወደሚገኝበት ሊዝበን ካመራ በኋላ የነበረው ቆይታው ከባድ ቢሆንም እሱ ግን እጅ ሳይሰጥ ነገው ላይ ብቻ አተኩሮ ጠንክሮ መሥራቱን ቀጠለ።