በአሜሪካ 64 ሰዎችን ይዞ ሲበር የነበረ የመንገደኞች አውሮፕላን በሮናልድ ሬገን አየር ማረፊያ ለማረፍ ሲቃረብ ከጦር ሄሊኮብተር ጋር ተጋጭቶ መውደቁ ተገልጿ።
ቦምባርዲየር CRJ-700 የተሰኘው የሀገር ውስጥ የበረራ አውሮፕላን 60 ተሳፋሪዎችን እና አራት የበረራ አባላትን አሳፍሮ እንደነበር ነው የተገለፀው።
በአደጋው የመንገደኞች አውሮፕላኑ በፖቶማክ ወንዝ ውስጥ በመግባቱ የህይወት አድን ጀልባዎች እና ጠላቂዎች ፍለጋ ላይ መሆናቸው ተነግሯል።
አደጋ የደረሰበት የመንገደኞች አውሮፕላኑ መነሻውን ከዊቺታ ካንሳስ አድርጎ መዳረሻውን ወደ ዋሽንግተን እንደነበር ተገልጿል።
ከአውሮፕላኑ ጋር የተጋጨው የጦር ሄሌኮብተር ደግሞ ሶስት የአሜሪካ ጦር ወታደሮችን ይዞ እንደነበር የመከላከያ ባለስልጣን ተናግረዋል።
ስለአደጋው ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን ፕሬዝዳንቱ በሰጡት መግለጫ “በመጀመሪያ ምላሽ ሰጪዎቻችን እየሰሩት ላለው አስደናቂ ስራ እናመሰግናለን፣ ሁኔታውን እየተከታተልን ሲሆን ተጨማሪ ዝርዝሮችን እንሰጣለን” ሲሉ ተናግረዋል።
የአደጋውን ምክንያት እና ዝርዝር ጉዳዮች አስመልክቶ የአሜሪካ ፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ምርመራ እያካሄድኩ ነው ብሏል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።#Ebc
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ