የሥራ አመራር ቦርዱ በ2ኛ መደበኛ ስብሰባ የተቀመጡትን ዉሳኔዎች አፈጻጸም በዝርዝር በመገምገምና አስተያየት በመስጠት በዕለቱ በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
ቦርዱ በዛሬ ዉሎ በመጀመሪያ አጀንዳነት የተወያየዉ የሚዲያ ኔትወርኩ ተቋማዊ መዋቅር፣የሥራ መደቦች ተፈላጊ ችሎታና የሥራ ደረጃ ላይ የቀረበዉ ጥናት ተወያይቶ አጽድቋል።
ቦርዱ በሁለተኛ አጀንዳነት የመከረዉ የተቋሙን የሰዉ ኃይል ማሟላትን በተመለከተም ኢንዱስትሪዉ የሚፈልገዉን ዕዉቀት ባገናዘበ ና ህብረ ብሄራዊነትን ባከተተ መልኩ በጥንቃቄ እንዲፈጽም ወስኗል።
የሚዲያ ኔትወርኩ በሦሥተኛው አጀንዳነት የተወያዩ የሚዲያ ኔትወርኩ መሪ ሀሳብ(Motto)፣አርማና ሌሎች ተያያይዥ ጉዳዮችና በቀጣይ መሰራት ያለባቸዉ ላይ ተወይይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል።
ክልል መ/ኮ/ጉ/ቢሮ
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ