በአሜሪካ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ በኾነችው ሎስ አንጀለስ አካባቢ ሰሞኑን የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት እስከ አኹን የ24 ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። 13 ሰዎች የት እንደደረሱ አልታወቀም። እስከ አኹን 12 ሺሕ የሚኾኑ ቤቶችን አውድሟል። አንዳንድ መንደሮችን ወደ አመድነት የቀየረው ሰደድ እሳት፣ የፈጥረው ውድመት፣ እጅግ አስደንጋጭ ኾኗል።
የእሳት አደጋ ሠራተኞች አኹንም እሳቱን ለመቆጣጠር ብርቱ ጥረት ማድረጋቸውን ቀጥለዋል። እሳቱን ያባባሰው ደረቅ ነፋስ ተመልሶ ሊመጣ ይችላለ የሚል ስጋትም ተፈጥሯል።(VOA)
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ንግግር ለመጀመር አጥጋቢ እቅድ እንዳልደረሳት ገለጸች