ጥር 05 ቀን 2017 ዓ.ም፣ (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ)፥ የ4ኛ ዙር ተፋላሚዎችን ያሳወቀው አንጋፋው የኤፍ ኤ ካፕ ውድድር በተለይም ማንችስተር ዩናይትድን ከሌስተር ሲቲ ያገናኘው ድልድL ተጠባቂ ሆኗል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት የ3ኛ ዙር ጨዋታዎችን ያካሄደው የኤፍ ኤ ካፕ ውድድር 4ኛ ዙርን የተቀላቀሉ ክለቦችን የለየ ሲሆን የተጋጣሚ ቡድኖች ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡
በድልድሉ መሰረት በተለይም ማንችስተር ዩናይትድ ከሌስተር ሲቲ ጋር በኦልድትራፎርድ ያገናኘው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
በጊዝያዊነት ማንችስተር ዩናይትድን ሲመራ የቆየው የቀድሞ የክለቡ ታሪካዊ ተጨዋች ሩድ ቫን ኔስተሮይን በመተካት የቀያይ ሰይጣኖቹን ወንበር የተረከቡት አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ከሩድ ቫን ኔስትሮይ ጋር በሚያደርጉት የጥሎ ማለፍ ጨዋታ እንዳጓጓቸው ተናግረዋል፡፡
ቀበሮዎቹን የሚመራው ሩድ ቫን ኔስትሮይ የቀድሞ ክለቡን ለመፋለም ወደ ኦልድትራፎርድ ይመለሳል፡፡
ከሚጠበቁት የ4ኛ ዙር ጨዋታዎች መካከል ብራይተን በአሜክስ ስታድየም ቼልሲን የሚገጥምበት ጨዋታ ይገኝበታል፡፡
አሰልጣኝ ዌይን ሩኒን ካሰናበተ በኋላ በኤፍ ኤ ካፕ የ3ኛ ዙር ጨዋታ ድል የቀናው የሻምፒዮን ሺፑ ክለብ ፕለይ ማውዝ የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑልን ያስተናግዳል፡፡
በ4ኛው ዙር ከሜዳው ውጭ ጨዋታውን እንደሚያደርግ የተረጋገጠው ማንችስተር ሲቲ ከሌይተን ኦሬንት እና ደርቢ ካውንቲ አሸናፊ ጋር የሚጫወት ይሆናል፡፡
የ4ኛ ዙር ጨዋታዎች በቀጣይ ወር መጀመርያ ሰሞን ላይ እንደሚካሄዱ የወጣው መርሀ ግብር ያመለክታል፡፡
More Stories
የዱባይ ማራቶን በኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ፍጹም የበላይነት ተጠናቀቀ
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሠራተኞች መካከል የነበረው አለመግባባት በውይይት መፈታቱ ተገለጸ
በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን አማን ከተማ ለቢስት ባር እሮጣለሁ በሚል መሪ ቃል የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ