የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የደን አከባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ከናቡ እና መልካ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ጋር በጋራ በመሆን በሸካ ዞን ያለውን የባዮስፌር ሪዘርቭ ጥናት እንዲደረግ የውይይት መድረክ በቴፒ ከተማ አካሂዷል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ዞኑ በደንና ብዝሃ ህይወት የተከበበና ለመኖር ምቹ መሆኑን ጠቁመው ህብረተሰቡ ሀገር አቀፍ ባህላዊ የደን አጠባበቅን ወደ ዘመናዊ በማሻገር በጋራ በመጠበቅ መቆየቱን ተናግረዋል።
በአለምአቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ በኢትዮጵያ እንደ ሀገር ከተመዘገበው አንዱ የሸካ ዞን ጥቅጥቅ ደን በመሆኑ የመልካ ኢትዮጵያ ባደረገው ድጋፍ የሸካ ዞን አሁናዊ ባዮስፌርቭ ጥናት እንዲደረግ ለተደረገው ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን አከባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኢንጂነር አስራት ገ/ማሪያም እንደገለፁት በዩነስኮ ከተመዘገቡ ክልሎች መካከል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አንዱ ሲሆን እነሱም የሸካ ባዮስፌርቭና የካፋ ባዮስፈር መሆኑን ገልፀው የሸካ ባዮስፌር ሪዘርቭ ከተመዘገበ 12 ዓመት ያስቆጠረ ሲሆን አሁን ላይ እድሉን አግኝቶ የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።
አባቶች እስካሁን ጠብቀው ያደረሱትን ሀብት ምሁራን ሳይበረዝ ደግፈው ለትውልድ ማሻገር እንደሚገባቸውና ከሌሎች አካባቢዎች ለየት የሚያደርገው ጥብቅ ደን ያለው በመሆኑ ደንን ለመጠበቅ በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የፀደቀ ህግ መውጣቱንና የካርቬን ክፍያም ለማህበረሰቡ እንደሚፈፀምና ለቀጣይም በክልሉ ሌሎች ባዮስፌርቭ እንደሚመዘገብም ተገልጿል።
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።