ውድድሩ እየተካሄደ የሚገኘው በሸካ ዞን ስፖርት ምክር ቤትና የዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አዘጋጅነት መሆኑንም ተጠቁሟል ።
የዘንድሮው የ2017 የሸካ ዞን የባህል ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ባህላዊ ስፖርቶቻችን ለአንድነታችንና ለሰላማችን በሚል መርህ ቃል እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል ።
በዚህም በዞኑ የሚገኙ ሶስት ወረዳዎችና ሁለት ሁለት ከተማ አስተዳደሮች መካከል በአስራ ሶስት የስፖርት አይነቶች በማሻ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም ውድድር መካሄድ ጀምረዋል ።
በውድድር መረሃ ግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት
የሸካ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊና የዞን አስተዳደር ተወካይ አቶ ዳንኤል አድራሮ ክልላችን እንደ አዲስ ከተቋቋመ ወድህ ለተከታታይ ሶስት ዓመት በባህል ስፖርት ውጤታማ እንደሆነ በመግለፅ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል ።
የማሻ ከተማ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መልካም እንደሻው ስፖርት የሠላም ችቦ የሚለኮስበት የአንድነትና የወዳጅነት ስሜት የሚንፀባረቅበት እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የሚጠናከርበት ነው ብለዋል።
የሸካ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምርያ ተወካይ አቶ ብርሀኑ አዋሾ በዞናችን ባህላዊ ስፖርቶች ዘላቅና ቀጣይነት ያለው ሆኖ ለትውልድ እንድተላለፍ ለማድረግ የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል ውድድር ማካሄድ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።
በውድድሩ የአንዱን ባህልና ወግ እንድሁም ትውፊት እንዲያውቅና እንዲያስተዋውቅ ዕድል የሚፈጥር ከመሆኑም ባለፈ የወንድማማችነትና ህታማማችነትን ስሜት የሚያሳድግ መሆኑንም ገልፀዋል ።
የውድድር አዘጋጅ ኮሚቴዎች በበኩላቸው በቀጣይ በክልል ደረጃ በኮንታ ዞን አመያ ከተማ በሚካሄደው የ2017 ዓ.ም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የባህል ስፖርቶችና የባህል ፌስቲቫል ዉድድር ላይ ዞኑን የሚወክሉ ተወዳዳሪዎችን ለመመልመል ምቹ አጋጣሚ እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል።
ውድድሩ ለተከታታይ አምሰት ቀናት በማሸ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም እንደምካሄድም ተገልጾዋል።
የመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ የዞን፣ የወረዳ ፣የከተማ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ስሆን የዘንድሮ የባህል ስፖርቶችና የባህል ፌስቲቫል ዉድድር በ218 ተወዳዳሪዎች መካከል በአስራ አንድ ስፖርት አይቶች እንደሚደረግም ተጠቁሟል
More Stories
በኤፍ ኤ ካፕ 4ኛ ዙር ድልድል ሩበን አሞሪም ከሩድ ቫን ኔስትሮይ አገናኝቷል
የዱባይ ማራቶን በኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ፍጹም የበላይነት ተጠናቀቀ
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሠራተኞች መካከል የነበረው አለመግባባት በውይይት መፈታቱ ተገለጸ