January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በፈረንጆቹ 2025 መባቻ ብሪክስ ዘጠኝ ሀገራትን በአባልነት እንደሚቀበል ተገለፀ፡፡

በሶስት አህጉራት የሚገኙት አዲስ አባል ሀገራቱ ቤላሩስ፣ ቦልቪያ፣ ኢንዶኖዥያ፣ ካዛኪስታን፣ ኩባ፣ ማሌዥያ፣ ታይላንድ፣ ኡጋንዳ እና ኡዝቤከስታን መሆናቸው ታውቋል፡፡

የአዲስ አባል ሀገራቱ የአባልነት ጥያቄ ቀደም ሲል በሩሲያ ካዛን በተካሄደው 16ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ መፅደቁ ነው የተገለፀው፡፡

የብሪክስ አባል ለመሆን ከ30 በላይ ሀገራት ጥያቄ አቅርበው እንደነበር የተገለፀ ሲሆን አዲሶቹ ዘጠኝ አባል ሀገራቱ በብሪክስ መሪዎች ተገምገመው የአባልነት ጥያቄቸው ተቀባይነት ማግኘቱ ተመላክቷል፡፡

በቅርቡም ተጨማሪ አራት ሀገራት ብሪክስን ይቀላቀላሉ ተብሏል፡፡

በብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ የተመሰረተው የብሪክስ የኢኮኖሚ ቡድን በፈረንጆቹ 2024 ኢትዮጵያን ጨምሮ አራት ሀገራትን በአባልነት መቀበሉ ይታወሳል።

አዳዲስ አባል ሀገራት መቀላቀላቸውን ተከትሎም 9 አባላት የነበሩት ብሪክስ የኢኮኖሚ ቡድን የአባላቱን ቁጥር ወደ 18 ከፍ ማድረጉን ኢራን ፕሬስ እና አር ቲ ዘግበዋል፡፡