December 18, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በማሻ ወረዳ ጋቲሞ ቀበሌ ትምህርት ቤት ግቢ በ1 ሄክታር መሬት ላይ የለማው የበጋ መስኖ ስንዴ ከ200,000 ሺህ ብር በላይ ገቢ ማስገኘቱን ተገለፁ።

በሸካ ዞን ማሻ ወረዳ በጋቲሞ ቀበሌ 1ኛ ደረጃ እና መለስተኛ ት/ት/ቤት ውስጥ 1 ሄክታር መሬት ላይ የበጋ መስኖ ስንዴ በማልማት ከ30 ኩንታል በላይ ምርት በመሰብሰብና ከዚህም ሁለት መቶ አስር ሺህ ብር ገቢ መገኘቱን ትምህርት ቤቱ አስታውቋል።

የማሻ ወረዳ ግብርና አከባቢ ጥበቃ ህብረት ስራ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ልሳኑ አለማየሁ እንደገለፁት በ2016 በተዘጋጀው የበጋ መስኖ ስንዴ ንቅናቄ በርካታ ተግባራት በሁሉም አደረጃጀት መሰራታቸውና ብዙ ት/ቤቶች የውስጥ ገቢያቸውን ለማሳደግና በህብረተሰብ ተሳትፎ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አብራርተዋል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ መስፉን አዳሾ በበኩላቸዉ በወረዳው በ2016 ዓ.ም በበጋ መስኖ ስንዴ በሁሉም ቀበሌ አበረታች ውጤቶች እየመጡ በመሆናቸው የተጀመሩት የበጋ መስኖ ስንዴ አጠናክሮ በማስቀጠል የሀገራችንን ኢኮኖሚ ልናደርግ ይገባልም ብለዋል።

ምርቱ በጊዜ ተወቅቶ ለገበያ ቢቀረብ የተሻለ ገቢ ማግኘት እንደሚቻል እና በማሽን እጥረት በመቆየቱ በቀጣይ መሰል ተግዳሮቶችን በመቅረፍ የተሻለ ገቢ እንዲገኝበትና ተሞክሮዎችንም ለማስፋፋት እንደሚሰራ ጭምር ተገልጿል ።