December 18, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሩሲያ በዩክሬን ኢነርጂ መሰረተ ልማቶች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ፈጸመች

ማሻ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2017 ሩሲያ በዩክሬን ኢነርጂ መሰረተ ልማቶች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች፡፡

ጥቃቱ ከቀናት በፊት ዩክሬን በሩሲያ ታጋኖርግ ግዛት ለፈጸመችው የሚሳኤል ጥቃት አጸፋ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው÷ዩክሬን ወታደራዊ አቅሟን ለማጠናከር በምትጠቀምበት የነዳጅና የኢነርጅ መሰረተ ልማቶች ላይ የተሳካ ጥቃት ተፈጽሟል፡፡

የዩክሬን ኢነርጂ ሚኒስትር ጀርማን ጋሉሸንኮ በበኩላቸው÷የሀገሪቱ የሃይል መሰረተ ልማት ሞስኮ በፈጸመችው ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱን ተናግረዋል፡፡

ጥቃቱ ያደረሰውን ፍንዳታ ተከትሎ የሚፈጠረውን የጎንዮሽ ጉዳት ለመቀነስ ባለሞያዎች ርብርብ እያደረጉ እንደሚገኙ መጠቆማቸውንምአር ቲ ዘግቧል፡፡

በሌላ በኩል በማህበራዊ ትስስር ገጾች የተሰራጩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች እንደሚያሳዩት÷በዩክሬን ኦዴሳና ኢቫኖ ፍራንኮቮስክ አካባቢ ከፍተኛ የፍንዳታ ድምጽ ከተሰማ በኋላ በአካባቢው የሚገኙ የሃይል መሰረተ ልማቶች በእሳት ተያይዘዋል፡፡