January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከ18 ሚልየን ብር በላይ ወጪ በዞኑ ዋና ከተማ ቴፒ የተገነባው ህንፃ ግንባታው ተጠናቆ ርክክብ ተደረገ።

የሸካ ዞን ከተማ ልማትና የኮንስትራክሽን መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ካዳኔ ከስቶ እንደገለጹት ህንፃው በ2008 ዓ /ም ተጀምሮ በአከባቢው በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ግንባታው ዘጠኝ አመታትን የፈጀ መሆኑን ገልፀዋል።

ለግንባታው ወጪ ከ18 ሚሊዮን 7 መቶ ሺህ ብር በላይ ወጥቶለት መገንባቱ ተገልጸዋል።

የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ በላቸው ጀመረ በበኩላቸው ህንፃው መገንባቱ የፍርድ ቤቱን አገልግሎትን ቀልጣፋ ለማድረግ ሚናው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

ለህንጻው ግንባታው መጓተት የፋይናንስ እጥረትና በአካባቢው የተፈጠረ የጸጥታ ችግር ተጽዕኖ መፍጠሩን ኘሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

ግንባታውን ያከናወነው የአልሳም ኮንስራክሽን ስራ አስኪያጅ ኢኒጂነር ጀማል አሊ ህንጻው በተለያዩ ምክንያቶች የተጓተተ ቢሆንም አሁን ላይ ተጠናቋል ለአገልግሎት በቅቷል ሲሉ በርክክቡ ወቅት ገልጸዋል።

በህንጻው ርክክብ ላይ የተገኙት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ እንደተናገሩት የተጀመሩት ግንባታዎች መጠናቀቃቸው ለዞኑ የሚያበረክተው አስተዋፆ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረው ለህዝብ ጥራትና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ሚናው የጎ ነው ብለዋል።

የትኛውም ልማት በመተጋገዝና በመተባበር እንዲሁም አንዱ የጀመረውን አንደኛው የማጠናቀቅ ተግባር የዱላ ቅብብሎሽ ስራ በመሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጥል አለበት ብለዋል።