ማሻ፡ ታህሳስ 04/2017 ዓ.ም ማንቸስተር ሲቲ በእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ ከፍተኛ የተባለ ዓመታዊ ገቢ ማግኘቱ ተገልጿል።
ባለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት የሊጉን ዋንጫ በማንሳት አዲስ ታሪክ ማፃፍ የቻለው ማንቸስተር ሲቲ በ2023/24 የውድድር ዓመት 715 ሚሊዮን ፓውንድ ገቢ ማግኘቱ ይፋ ተደርጓል።
የክለቡ ገቢ ከባለፈው ዓመት ገቢ በ2.2 ሚሊዮን ፓውንድ ጭማሪ ማሳየቱ ተነግሯል።
ክለቡ በዓመቱ ውስጥ የሁሊያን አልቫሬዝ፣ ጇኦ ካንሴሎን እና ሊያም ዴላፕን ዝውውር ሳይጨምር ከተጫዋቾቹ ሽያጭ 139 ሚሊዮን ፓውንድ ገቢ ማግኘቱ ተሰምቷል።
በተጨማሪም በጨዋታ ቀን 756 ሚሊዮን ፓውንድ ገቢ ማግኘቱ ሲገለፅ ከባለፈው ዓመት አንፃር የ3.7 ሚሊዮን ፓውንድ ጭማሪ አሳይቷል።
የእንግሊዙ ክለብ በአጠቃላይ በዓመቱ ውስጥ ከታክስ በፊት 73.8 ሚሊዮን ፓውንድ ትርፍ አግኝቻለሁ ብሏል።
More Stories
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊቨርፑል ከአስቶን ቪላ ጋር ይጫወታሉ
የቀድሞው የሪያል ማድሪድ ኮከብ ማርሴሎ ጫማ ሰቀለ
አርሰናል ከካራባኦ ዋንጫ ተሰናበተ