የዳበረ እና ሁሉን አቀፍ የዴሞክራሲ ስርዓት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገልጸዋል፡፡ ዳይሬክተር ጀነራሉ ዳያስፖራው በሀገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ ያለውን ተሳትፎ ሊያጠናክር እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በኳታር ዶሃ ተከብሯል፡፡ በመርሃ-ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት አምስት ዓመታት ለሀገሪቱ ቀጣይ ጉዞዎች መሰረት የሚጥሉ በርካታ ሥራዎችን ማከናወኑን አንስተዋል፡፡ መንግሥት ልዩነቶች የግጭት መንስኤ እንዳይሆኑ እና በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አቋቁሞ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በቀጠር፣ የመን እና ኢራን የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፈይሰል አልይ አብራሂም በበኩላቸው ፤ ብልፅግና ፓርቲ ዳያስፖራው በሀገሩ ልማት ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን የተለያዩ ዕድሎችን መክፈቱን አውስተዋል፡፡ ዳያስፖራው በተለይ በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በቱሪዝም፣ በክህሎት፣ በዕውቀት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፎች ያሉ ዕድሎችን በአግባቡ መጠቀም እንዳበትም ማስገንዘባቸውን በዶሃ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
EBC
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።