በኦሮሚያ ክልል መንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሰላም ስምምነት በመፈጸማቸው የሰራዊቱ አባላት ወደ ካምፕ መግባት መጀመራቸው ይታወቃል።የኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፤ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሰላም አማራጭን በመቀበሉ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው ገልጿል።በጫካ የቀሩ የሰራዊቱ አባላትም ፈጥነው ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጡም ጥሪውን አስተላልፏል።ሰላም እንዲሰፍን የሃይማኖት አባቶች ጸሎት እና ምህላን ሲያደርጉ እንደነበር ያስታወሰው መግለጫው፤ በቀጣይነትም ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ጉባኤው የሰላም ግንባታ ላይ አበክሮ እንደሚሰራ አረጋግጧል።
ፋና
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ