ዛሬ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል በአድዋ ድል መታሰቢያ ፓን አፍሪካንዚም አዳራሽ “ሀገራዊ መግባባት ለህብረብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ባማረና በደመቀ ሁኔታ አክብረናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፤ በዓሉ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ቤት፣ የኢትዮጵያውያን ሁሉ መናገሻ፣ የአፍሪካ ህብረት መዲና እና ሶስተኛዋ የዓለም ዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ የህብረብሄራዊ አንድነታችን ተምሳሌት መሆኗን በሚመጥን ልክ ተከብሯል ብለዋል። በበዓሉ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር እና የሁሉም ክልሎች አፈ ጉባኤዎች መገኘታቸውንም ጠቅሰዋል፡፡
EBC
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።