January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የባህልና ቱሪዝም ኤግዚቢሽን እና ፌስቲቫል በአርባ ምንጭ ከተማ በይፋ ተከፈተ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የባህልና ቱሪዝም ኤግዚቢሽን እና ፌስቲቫል በአርባ ምንጭ ከተማ በይፋ ከፍተዋል። 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ዋዜማ በአርባ ምንጭ ከተማ በተለያዩ ዝግጅት እየተከበረ ይገኛል። የበዓሉ አካል የሆነው 32 ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የየራሳቸው ቅርስ እና ባህላዊ ቁሶችን የሚያስጎበኙበት ባህላዊ ፌስቲቫል ዛሬ ተጀምሯል፡፡ 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በተለያዩ ስያሜዎች የሚከበር ሲሆን ህዳር 26 የደቡብ ኢትዮጵያ ቀን በመባል ይከበራል፡፡

EBC