የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በወቅታዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም፤ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ የ24 አገራት አዲስ አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ በጽ/ቤታቸው መቀበላቸውን ተናግረዋል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ አምባሳደሮቹ አገሮቻቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በቆይታቸው እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን አምባሳደር ነብያት ገልጸዋል። ቃል አቀባዩ በኢትዮጵያ አዲስ ኤምባሲ የከፈቱ አገራት አምባሳደሮችም የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንቱ ማቅርባቸውን እና ለአብነት ያህል ስሎቬኒያ አምባሳደር ተጠቃሽ መሆናቸውን አንስተዋል።
EBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።