January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ትራምፕ የጋዛ ታጋቾች በፍጥነት ካልተለቀቁ በመካከለኛው ምስራቅ “ከባድ ችግር” ይፈጠራል አሉ

ትራምፕ “ታጋቾቹ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆኜ ቢሮ ከምገባበት ከጥር 20፣2025 በፊት ካልተለቀቁ በመካከለኛው ምስራቅ ከባድ ችግር ይፈጠራል፤ይህን ግፍ የፈጸሙትም ከባድ ቅጣት ይጠብቃቸዋል” ብለዋል።ትራምፕ አክለውም እንዳሉት “ይህን ግፍ የፈጸሙ በረጅሙ የአሜሪካ ታሪክ ማንም ከተመታው በላይ በከባዱ ይመታሉ።”ሀማስ ታጋቾቹን ለመልቀቅ ከመስማማቱ በፊት ጦርነቱ እንዲቆም እና የእስራኤል ጦር ከጋዛ እንዲወጣ ጠይቋል።

Al-Ain