ኢትዮጵያ እና ሳውዲ አረቢያ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ተስማምተዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ኢ/ር ዋሊድ አብዱልከሪም አልኩራይጂ ጋር በሪያድ ምክክር አድርገዋል። ሁለቱ ወገኖች በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እና በሁለትዮሽ እና በአለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ትብብር በማድረግ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ተስማምተዋል። በውይይቱ ሁለቱም ወገኖች የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እና ረቂቅ ስምምነቶችን ተግባራዊ ለማድረግ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል
#EBC
More Stories
ህብረተሰቡን በማህበራዊና ኢኮኖም ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ እየተደረገ ያለውን ጥረት ሁሉም ልደግፍ እንደምገባ የሸካ ህዝቦች ልማት ማህበር ገለፀ።
የሸካ ህዝቦች ልማት ማህበር 11ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ መካሄድ ጀምሯል
የዘመናት የማሻ ከተማና አካባቢው ህዝብ ጥያቄ የነበረው የመብራት አቅርቦት ችግር የሚፈታ የሳብስቴሽን ግንባታ አልቆ መብራት የማብራት ሙከራ ስራ በስኬት ተጠናቀቀ