January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝም ና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር በዓለም ለ45ኛ በኢትዮጵያ ለ37ኛ በክልሉ ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረዉ የዓለም የቱሪዝም ቀን ”ቱሪዝም ለሰላም” በሚል መር ቃል በቦንጋ ከተማ እየተከበረ ነዉ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢነንጅነር ነጋሽ ዋገሾ ቱሪዝም ከሀገሪቱ ኢኮኖሚ ያለዉን ድርሻ ለማሳደግ ባለፉት ጥቅት አመታት በተሰሩት ስራዎች መነቃቃት እየታዬ መሆኑን ገልፀዋል።ክልሉ የተለያዩ የቱሪስት መስህቦች ባለበት ቢሆንም እነዚህን ሀብቶች ለማስተዋወቅና ከዘርፍ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለመጠቀም የመሰረተ ልማት ችግር የጠቆሙት አቶ ፋንታሁን የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ የቱሪዝም ልማት ንቅናቄ በማካሄድ የዘርፉን ስብራት መጠገን እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል ።

በቸርነት አባተ