በጉባዔው መክፈቻ ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ባደረጉት ንግግር፤ የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እየተሸጋገር መሆኑን ገልጸዋል። ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አመራር ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ማድረጓን በመግለጽ፤ በዚህም ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ባደረጉት ንግግር የኢትዮ-ቻይና ግንኙነት በሁኔታዎች የማይለወጥ ስትራቴጂክ አጋርነት መድረሱን እና የዛሬው ጉባዔም በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር መሆኑን ገልጸዋል።
#EBC
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ