November 15, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የቴፒ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የከተሞች ፕላን ኢኒስቲትዩት ተገለጸ፡፡

የከተማ ልማት ለማረጋገጥና የአቅርቦትና ፍላጎት መመጣጠን በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ለተለያዩ አገልግሎቶች ሚቹ የሆነ ከተማ መፍጠር ያስፈልጋል ተብለዋል።የከተማ መዋቅራዊ ፕላን ከሁሉ አስቀድሞ እጅጉን አስፈላጊ መሆኑን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የከተሞች ፕላን ኢኒስቲትዩት ላነርር እና የቴፒ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ፕሮጀት አስተባባሪ አቶ ታከለ ጉበላ ገልጸዋል። የከተማዋን ስትራቴጂካዊ ፕላን ወደ መዋቅራዊ ፕላን ወይም የከተማውን የቆዳ ስፋት ከነበረበት 2 ሺ 5 መቶ ሄክታር ወደ 6ሺ5 መቶ 60 ሄክታር በማሳደግ የነበረዉን ፕላን መከለስና የተለያዩ ተግባራት በጥልቀት እየተከናወነ አብዛኛዉ ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ብለዋል ።

ዘጋቢ ጌትነት ገረመዉ

You may have missed