ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 29) ላይ ለመሳተፍ አዘርባጃን ባኩ ገብተዋል፡፡ፕሬዚዳንቱ ሀይደር አሊየቭ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአዘርባጃን ጤና ሚኒስትር ቴይሙር ሙሴየቭን ጨምሮ በከፍተኛ ሃላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡”በጋራ ለአረንጓዴ ምድር” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው የኮፕ29 ጉባዔ ኢትዮጵያ በተራቆተ መሬት የደን ሽፋንን መልሶ ለማልማት የወሰደችውን ቁርጠኝነት እና ዘላቂነት ያለው የመሬት አጠቃቀም ተሞክሮዋን እንደምታቀርብ ይጠበቃል።ኢትዮጵያ የጀመረችው የአረንጓዴ አሻራ ልማት ኢኒሼቲቭ በተለይ በግብርና፣ በኢኮ-ቱሪዝምና በታዳሽ ሀይል ላይ እየተሰራ ያለው ስራ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሚገኝም ይታወቃል።
al-Ain
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።