ዩን ሱክ የል ከሰሞኑ ከስምንት አመት በኋላ ወደ ጎልፍ መጫወቻ ስፍራ በማቅናት ልምምድ የጀመሩት በቀጣይ ከትራምፕ ጋር ሲገናኙ ለመጫወት ነው ተብሏልቀዳሚ ገፅዜናአስተያየትፖለቲካኢኮኖሚማህበራዊልዩልዩስፖርትየመረጃ ሳጥንተመልከትፖለቲካየደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ከትራምፕ መመረጥ በኋላ የጎልፍ ጨዋታ ልምምድ ጀመሩዩን ሱክ የል ከሰሞኑ ከስምንት አመት በኋላ ወደ ጎልፍ መጫወቻ ስፍራ በማቅናት ልምምድ የጀመሩት በቀጣይ ከትራምፕ ጋር ሲገናኙ ለመጫወት ነው ተብሏልአል-ዐይን Published on: 2024/11/12 10:04 EAT Last updated on: 2024/11/12 10:05 EATየአሜሪካው አዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው የሁለቱን ኮሪያዎች ውጥረት ለማርገብ መሞከራቸው ይታወሳልየደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ዮን ሱክ የል የጎልፍ ጨዋታ ልምምድ ማድረግ ጀመሩ።ፕሬዝዳንቱ ወደ ጎልፍ መጫወቻ ስፍራ በማቅናት ልምምድ የጀምሩት በ2024ቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ነው።የፕሬዝዳንት ዮን ሱክ የል ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫም ፕሬዝዳንቱ ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ጎልፍ መጫወቻ ስፍራ ያቀኑት ከስምንት አመት በፊት በ2016 እንደነበር ገልጿል።“በርካታ ለትራምፕ ቅርበት ያላቸው ሰዎች እኔና ትራምፕ በአጭር ጊዜ የምንግባባ እንደሆንን ይነግሩኛል” ያሉት ፕሬዝዳንት ለተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ስልክ ደውለው ደስታቸውን ገልጸውላቸዋል።ትራምፕ “ማራላጎ” በተሰኘውና ፍሎሪዳ በሚገኘው ቅንጡው መዝናኛ እና መኖሪያቸው ውስጥ ጎልፍ እንደሚያዘወትሩ ይታወቃል።የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ከስምንት አመት በኋላ ወደ ጎልፍ ልምምድ ስፍራ መመለስም ትራምፕ በሴኡል ጉብኝት ሲያደርጉም ሆነ እርሳቸውም ወደ አሜሪካ ለጉብኝት ሲያቀኑ አብረው ለመጫወት ያለመ ነው ተብሏል።ደቡብ ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር ያላትን ወዳጅነት ለማጠናከር ከትራምፕ ጋር ጓደኛ መሆን እንደ አንድ መሳሪያ ለመጠቀም ያሰቡት ዮን ሱክ የል ከሪፐብሊካኖች ጋር የሀገራቱን ትብብር ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እየመከርን ነው ማለታቸውንም ሬውተርስ ዘግቧል።አሜሪካ የደቡብ ኮሪያ ኩባንያዎች ዋነኛ የንግድ ማዕከል መሆኗ ይታወቃል። በመጀመሪያው የትራምፕ የስልጣን ዘመን (ከ2017 እስከ 2021) በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ 28 ሺህ 500 የአሜሪካ ወታደሮች ወጪ መጋራት ጉዳይ ሀገራቱን በተደጋጋሚ ሲያጋጭ እንደነበር የሚታወስ ነው።
Al-Ain
More Stories
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን ጋር የሚያደርጉት ንግግር እየተመቻቸ መሆኑን ገለጹ።
የአሜሪካ ኮንግረስ በአለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ድምጽ ሰጠ
አስደንጋጩ የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት አልበረደም