በአዲሱ የሩብን አሞሪም የረዳት አሰልጣኞች ስብስብ ውስጥ ቦታ ያላገኘው ቫኒስትሮይ ቡድኑን ለቋል
አል ዐይን ኒውስቀዳሚ ገፅዜናአስተያየትፖለቲካኢኮኖሚማህበራዊልዩልዩስፖርትየመረጃ ሳጥንተመልከትስፖርትሩድ ቫንኒስትሮይ ከማንችስተር ዩናይትድ ተሰናበተበአዲሱ የሩብን አሞሪም የረዳት አሰልጣኞች ስብስብ ውስጥ ቦታ ያላገኘው ቫኒስትሮይ ቡድኑን ለቋልአል-ዐይን Published on: 2024/11/12 10:30 EATቫንኒስትሮይከ12 ቀናት በኋላ ቡድኑን በመምራት የመጀመርያውን ጨዋታ የሚያደርገው ሩብን አሞሪም ማንችሰተር ደርሷልየኤሪክ ቴን ሀግን ከዩናይትድ መሰናበት ተከትሎ ቡድኑን ያለፉትን አራት ጨዋታዎች በጊዜያዊ አሰልጣኝነት የመራው ሩድ ቫኒስትሮይ ከቡድኑ ለቋል፡፡ሩድ ቫን ኒስቴልሮይ በአዲሱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የረዳት አሰልጣኞች ስብስብ (ኮቺንግ ስታፍ) ውስጥ ሚና አለማግኝቱን ተከትሎ ነው ቡድኑን የለቀቀው፡፡የ48 አመቱ ኔዘርላንዳዊ የሀገሩ ልጅ ኤሪክ ቴን ሃግ ከሃላፊነት ከተነሱ በኋላ የኦልድትራፎርድ ሀላፊነቱን በጊዜያዊነት በመረከብ ካደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ሶስቱን አሸንፎ አንድ አቻ በመውጣት በውጤት ድብርት ውስጥ የነበረውን ዩናይትድ ማነቃቃት ችሏል፡፡በተጨዋችነት ዘመኑ አምስት የውድድር አመታትን በኦልትራፎርድ ያሳለፈው ኔዘርላንዳዊው አጥቂ በረዳት አሰልጣኝነት ለሁለት አመት ለመቆየት ባሳለፍነው ሀምሌ የፈረመው ኮንትራት በአሞሪም ተቋርጧል፡፡ ክለቡ ቫንኒስትሮይ መውጣቱን ባረጋገጠበት መግለጫ “ሩድ ሁሌም የማንቸስተር ዩናይትድ ጀግና ነው ፤ላበረከተው አስተዋፅኦ እና ከክለቡ ጋር ባደረገው ቆይታ ሁሉ ሚናውን በተወጣበት መንገድ አመስጋኞች ነን ” ሲል ተናግሯል።ቢቢሲ ያነጋገራቸው የስፖርት ተንታኞች ደጋፊዎች ቡድኑን በማነቃቃት ጥሩ ተስፋ የሰጣቸውን ቫንኒስትሮይን መሰናበት በበጎ አልተቀበሉትም ብለዋል፡፡እስከ 2026 ድረስ የሚያቆየው ኮንትራት የነበረው አሰልጣኙ በዩናይትድ ረዳት አሰልጣኞች ዝርዝር ውስጥ ኮንትራቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የመቆየት ፍላጎት እንደነበረውም ገልጸዋል፡፡ሆኖም ሩበን አሞሪም የራሱ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ የአሰልጣኝ ቡድን ያለው እና በውስጡም ሰፊ የማንቸስተር ዩናይትድ ልምድ ላለው እና የራሱ የአመራር ፍላጎት ላለው ሰው ቦታ የለውም ተብሏል፡፡ከቫንኒስትሮይ በተጨማሪ ሶስት ሌሎች አሰልጣኞች ቡድኑን የለቀቁ ሲሆን ቀደም ሲል ከነበረው ኮቺንግ ስታፍ የሚቆየው የቀድሞ የቡድኑ አማካይ የነበረው ዳረን ፍሊቸር ብቻ መሆኑ ታውቋል፡፡ዩናይትድን ለቀጣዩ ሁለት አመት ተኩል ለመምራት ስምምነት የፈጸመው ፖርቹጋላዊው ሩብን አሞሪም በትላንትናው እለት በዩናይትድ ማሰልጠኛ ማዕከል ካሪንግተን ደርሷል፡፡ በስፍራው የክለቡ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኦማር ባራዳን ጨምሮ ሌሎች የክለቡ ሃላፊዎች አቀባበል ያደረጉለት ሲሆን በተጨማሪም የስልጠናማዕከሉን አዘዋውረው አስጎብኝተውታል፡፡የ39 አመቱ ወጣት አሰልጣኝ ከኢንተርናሽናል ብሬክ በኋላ ቡድኑ ከሜዳው ውጪ ዘንድሮ ሊጉን ከተቀላቀለው ኢፕስዊች ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ይመራል::
Al-Ain
More Stories
የአለም የማራቶን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበችው ሩት ቼፕንጌቲች የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የክብር እንግዳ ትሆናለች
ኢትዮጵያና ዑጋንዳ ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ
በፕሪሚየር ሊጉ ሊግ ማንቸስተር ዩናይትድ እና አስቶንቪላ አቻ ተለያዩ