January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በ2025 ምርጫ የሚያደርጉ ሀገራት እነማን ናቸው?

ከአፍሪካ ጋቦን፣ ማላዊ እና ኮቲዲቯር የሚያደርጉት ምርጫ ይጠበቃልበ2025 ጠቅላላ ምርጫ የሚያደርጉ ሀገራት እነማን ናቸው?በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ባሉ አብዛኞቹ ሀገራት በምርጫ አማካኝነት መንግስት ይመሰረታል፡፡ ይህን ተከትሎም በየዓመቱ በመላው ዓለም ባሉ ሀገራት በምርጫ ስልጣንን መቆጣጠር ተለምዷል፡፡ከሁለት ወራት በኋላ በሚመጣው የፈረንጆቹ 2025 ዓመት ውስጥ 29 ሀገራት ምርጫ የሚደርጉ ሲሆን ጀርመን፣ ሲንጋፖር፣ ፊሊፒንስ፣ ኖርዌይ፣ ጃፓን እና ሌሎችም ሀገራት ምርጫው ከሚካሄድባቸው ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡ከአፍሪካ ታንዛኒያ፣ ኮትዲቯር፣ ካሜሩን፣ ማላዊ፣ ሲሸልስ፣ ጋቦን እና ሌሎችም ሀገራት የሕግ አውጪ ምክር ቤት አባላት እና ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡