የሩሲያ የወርቅ ክምችት ዋጋ በጥቅምት ወር ለመጀመሪያ ጊዜ ከ200 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማለፉን የሀገሪቱ ብሔራዊ ባንክ መረጃ ያመለክታልየሩሲያ የወርቅ ክምችት ዋጋ በታሪክ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ።የሩሲያ የወርቅ ክምችት ዋጋ ለመጀመሪያ ጊዜ በጥቅምት ወር ውስጥ ከ200 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያለፈ ሲሆን ሀገሪቱ በአለም አቀፍ ክምችት ያላት ድርሻ 32.9 በመቶ መጨመሩን የሩሲያው አርቲ የሀገሪቱን ብሔራዊ ባንክ መረጃ ጠቅሶ ዘግቧል።’ባንክ ኦፍ ሩሲያ’ የወርቅ ክምችት ዋጋው በ4 በመቶ ማደጉን እና ባለፈው መሰከረም ወር የተመዘገበውን ሪከርድ መስበሩን በትናንትናው እለት ባወጣው ሪፖርት ገልጿል። ባንኩ እንደገለጸው የክምችቱ ዋጋ እስከ ህዳር አንድ ድረስ 207.7 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።ባለፈው ጥቅምት ወር የወርቅ ዋጋ በ4 በመቶ የጨመረው አንድ አውንክ ሪከርድ በሰበረ 2800 ዶላር ከተሸጠ በኋላ ነው። የወርቅ ዋጋ በጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ምክንያት በቅርብ ጊዜያት ሲዋዥቅ ቆይቷል።የሩሲያ አለምአቀፍ የወርቅ ክምችት ጭማሪ 34 በመቶ ከተመዘገበበት ከህዳር 1999 ወዲህ ባለፈው ወር ነው ከፍተኛ ሆኖ የተመዘገበው። በአጠቃላይ በሀገሪቱ ዘመናዊ ታሪክ ከፍተኛ ሆኖ ተመዘገበው 59.9 በመቶ ጭማሪ በጥር 1993 ነው።የብሔራዊ ባንኩ መረጃ እንደሚያሳየው የሀገሪቱ አለምአቀፍ ክምችት ከባለፈው ወር በ2.1 ቢሊዮን ዶላር ቀንሶ እስከ ህዳር አንድ ድረስ 631.6 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። ግማሽ ገደማ የሚሆነው የሩሲያ የውጭ መጠባበቂያ ክምችት በ2022 መጀመሪያ ላይ ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ እንዳይንቀሳቀስ ተደርጓል። ባንኩ እንዳይንቀሳቀስ የተደረገውን ሀብት ሀብት በዝርዝር አላስቀመጠም።በሀገር ውስጥ የነበረው ወርቅ እና የውጭ ምንዛሬ እንዲሁም በቻይና የን የተቀመጠው ሀብት እግድ አልተጣለበትም።ሩሲያ ምዕራባውያን ሀብቷ እንዳይንቀሳቀስ ከማድረግ አልፈው ለመውረስ የሚያደርጉትን ጥረት እንደሌብነት እንደምታየው መግለጿ ይታወቃል። ‘የባንክ ኦፍ ሩሲያ’ ገዥ ኢልቪራ ናቢዩሊና ባንኩ የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ በተለያዩ ገንዘቦች ለማስቀመጥ ለአመታት መስራቱን እና ምዕራባውያን እንዳይንቀሳቀስ ያደረጉትን ሀብት ቢወርሱም ገበያ ተረጋግቶ ይቀጥላል ብለዋል።
al-ain
More Stories
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን ጋር የሚያደርጉት ንግግር እየተመቻቸ መሆኑን ገለጹ።
የአሜሪካ ኮንግረስ በአለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ድምጽ ሰጠ
አስደንጋጩ የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት አልበረደም