ተመራጩ ፕሬዝዳንት በካቢኔያቸው ውስጥ እነ ማንን ሊያካትቱ እንደሚችሉ መረጃዎች እየወጡ ናቸውዶናልድ ትራምፕ እነማንን ሊሾሙ ይችላሉ?ባሳለፍነው ማክሰኞ የተደረገው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጉዳይ አሁንም ዓለምን ትኩረት መሳቡን ቀጥሏል፡፡ከምርጫው ውጤት መታወቅ በኋላ አሸናፊው ዶናልድ ትራምፕ በሚመሰርቱት ካቢኔ ውስጥ እነማንን ሊያካትቱ ይችላሉ የሚለው ጉዳይ የሚዲያዎች ዋነኛ ትኩረት ሆኗል፡፡ዶናልድ ትራምፕ ጥር 6 ላይ ከተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በይፋ ስልጣን የሚረከቡ ሲሆን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖት ጥረቶች በመካሄድ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡በተለይም ዶናልድ ትራምፕ ቁልፍ በሚባሉ የመንግስታቸው ሀላፊነት ቦታዎች ላይ የሚያደርጓቸው ሹመቶች ተጠባቂ ናቸው፡፡ለአብነትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ መከላከያ ሚኒስትር፣ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር፣ የመንግስት ቃል አቀባይ፣ የስለላ ተቋማት እና ሌሎችም ተጠባቂ ናቸው፡፡ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ከታጩት መካከል በጀርመን የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ሪቻርድ ግሬኔል እና የፍሎሪዳው ሴናተር ማርክ ሩቢዮ ተጠብቀዋል፡፡ለመከላከያ ሚኒስትርነት ደግሞ የቀድሞው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ሲታጩ የ27 ዓመቷ ወጣቷ ካሮሊን ለቪት ደግሞ የነጩ ቤተ መንግስት ቃል አቀባይ እንደምትሆን ይጠበቃል፡፡ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን እንደያዙ ሊያደርጓቸው የሚችሉት ውሳኔዎች ምን ምን ሊሆኑ ይችላሉ?የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆነው ኢለን መስክ ደግሞ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር ውጤታማነት ሀላፊ ተደርገው ሊሾሙ እንደሚችሉ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡በዘንድሮው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ላይ በግል ተወዳዳሪነት የቀረቡት ኬነዲ ጁኒየር ደግሞ የአሜሪካ በሽታ መከላከል እና ቁጥጥር ሃለፊ እንዲሁም ቶምሆማን ደግሞ የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል፡፡የምርጫ ቅስቀሳ እቅድ ጠበብት ናቸው የሚባሉት ሱዚ ዊልስ ደግሞ የዶናልድ ትራምፕ መንግስት ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወይም ቺፍ ኦፍ ስታፍ ተደርገው እንደሚሾሙ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
Al-Ain
More Stories
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን ጋር የሚያደርጉት ንግግር እየተመቻቸ መሆኑን ገለጹ።
የአሜሪካ ኮንግረስ በአለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ድምጽ ሰጠ
አስደንጋጩ የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት አልበረደም