January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በ2017/18 የምርት ዘመን ከውጭ ከሚገዛው 23 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 472 ሺህ 500 ኩንታል ዩሪያ የጫነች የመጀመሪያዋ ኤም ቪ አባይ ሁለት የተሰኘች የኢትዮጵያ መርከብ ጂቡቲ ወደብ ደርሳለች።

በቀጣይ ቀናት ወደ ሀገር ውስጥ የማጓጓዝ ሥራውም በፍጥነት እንደሚጀመር ይጠበቃል። ለ2017/18 የምርት ዘመን የ23 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ለመፈጸም 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ተመድቧል። መንግሥት አዲስ የግዢ መመሪያ በማውጣቱ ባለፈው የምርት ዘመን 21 ቢሊዮን ብር ለማዳን መቻሉን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን መረጃ ያመለክታል።

#EBC