January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የዓድዋ ድል መታሰቢያ አዲስ አበባን የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ከተመረቀ ዕለት ጀምሮ ታላላቅ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ኮንፍፈረንሶችን በማስተናገድ አዲስ አበባን የኮንፈረንስና የስበት ማዕከል በማድረግ አይነተኛ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኝ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ “ከረሃብ ነጻ ዓለም ጉባኤ” በአዲስ አበባ በአድዋ ድል መታሰቢያ በጥሩ ሁኔታ ተካሂዶ ተጠናቅቋል ብለዋል። የዓድዋ ድል መታሰቢያ ከተመረቀ ዕለት ጀምሮ የዚህ አይነት ታላላቅ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ኮንፍፈረንሶችን በማስተናገድ መዲናዋን የኮንፈረንስና የስበት ማዕከል በማድረግ አይነተኛ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል። አዲስ አበባን የቱሪዝም፣ የኮንፈረንስ እንዲሁም የስበት ማዕከል ለማድረግ የሰራናቸው ስራዎች ፍሬ አፍርተው ታላላቅ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ኮንፍራንሶችን ማስተናገድ በመጀመራችን ደስተኞች ነን ሲሉም አክለዋል። በርትተን ስንሰራ ብዙ እጥፍ መልሶ እንደሚከፍለን ይህ አንዱ ማሳያ ነው ያሉት ከንቲበዋ፤ እነዚህ ኮንፈረንሶች በከተማችን እንዲካሄዱ ያቀዳችሁ፣ የሰራችሁ እና ያስተናገዳችሁ አካላትን በሙሉ በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ብለዋል።

EBC