ዓለም አቀፍ መሪዎችን፣ ባለሞያዎችን እና የጉዳዩ ተቆርቋሪዎችን በአንድ ላይ በማምጣት እንዲወያዩ በማድረግ የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የ”ከረሃብ ነጻ ዓለም” ጉባኤ ተሳታፊዎችን እንኳን ወደ አፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና በሰላም መጣችሁ ብለዋል።በኢትዮጵያ ባለፉት ሥድስት ዓመታት በግብርና ሽግግር እና ምርታማነት ላይ በማተኮር በተሰራው ስራ የታረሰ መሬትን እጥፍ በማድረስ፣ ከፍ ያለ እሴት ባላቸው የኢንደስትሪ አዝርዕት ምርት ላይ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መገኘታቸውን ጠቁመዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም በሚቀጥሉት ቀናት የጉባኤው ውይይቶች የጋራ ግቦቻችንን ስኬት የሚያፋጥኑ ታላላቅ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ እተማመናለሁ ብለዋል።
EBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።