January 28, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እለት በርካታ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈችፒዮንግያንግ በጥቂቱ ሰባት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሷን የጃፓን የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል

ኪም ጆንግ ኡን የሁለቱን ኮሪያዎች መሪዎች ያጨባበጡት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን እንዲመጡ ፍላጎት እንዳላቸው ተነግሯልአሜሪካ 47ኛ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫዋን በምታደርግበት በዛሬው እለት ሰሜን ኮሪያ በርካታ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን አስወንጭፋለች።የጃፓን የመከላከያ ሚኒስትር ጄን ናካታኒ እንደገለጹት ፒዮንግያንግ በጥቂቱ ሰባት አጭር ርቀት የሚምዘገዘጉ ሚሳኤሎችን ተኩሳለች።ሚሳኢሎቹ በ100 ኪሎሜትር ከፍታ እስከ 400 ኪሎሜትሮች መምዘግዘጋቸውንና በኮሪያ ልሳነ ምድር እና በጃፓን መካከል በሚገኝ ውሃማ ስፍራ መውደቃቸውንም ነው ሚኒስትሩ ያስታወቁት።የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴርም ጎረቤት ሰሜን ኮሪያ የሴኡልን ወታደራዊ ተቋማትና በሀገሪቱ የሚገኘውን የአሜሪካ የጦር ሰፈር ሊይጠቁ የሚችሉ ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏን ገልጿል።ፒዮንግያንግ የዛሬውን የሚሳኤል ሙከራ ያደረገችው ኪም ጆንግ ኡን አሜሪካ ድረስ ሊምዘገዘግ የሚችል “ሃውሶንግ-19” የተሰኘ አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳኤል ባስወነጨፈች በቀናት ልዩነት ነው።በሙከራው የተበሳጩት አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓንም ባለፈው እሁድ ግዙፍ የሶስትዮሽ የአየር ልምምድ ማድረጋቸው ይታወሳል።

Al-Ain