October 16, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያና ዑጋንዳ ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ውድድር ዛሬ ከዑጋንዳ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋል፡፡ለዛሬው ጨዋታ ዝግጅት ሲያደርግ የቆው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከትናንት በስቲያ እና ትናንት በታንዛኒያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስልጠና ማዕከል እና ኬ ኤም ሲ ስታዲየም ልምምዱን ሠርቷል፡፡በዛሬው ዕለትም በአዛም ኮምፕሌክስ ስታዲየም 12 ሠዓት ላይ የመጀመርያ የምድብ ጨዋታውን ከዑጋንዳ ጋር እንደሚደርግ የወጣው መርሐ-ግብር አመላክቷል፡፡

FBC