እስራኤል በጋዛ በከፈተችው መጠነሰፊ የአየር እና የእግረኛ ጦር ጥቃት 41825 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የፍልስጤም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያልእስራኤል በሀማስ ጥቃት አንደኛ አመት እለት ሊቃጣባት የሚችል ጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅ ላይ ነች።ይህ የሆነው እስራኤል ኢራን ለፈጸመችባት የሚሳይል ጥቃት ከባድ ምላሽ ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቋ በተገለጸበት ወቅት ነው።እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በሚገኘው የሄዝቦላ ይዞታ ላይ እያደረሰች ያለውን ጥቃት አጠናክራ ቀጥላለች። የሊባኖስ ብሔራዊ ዜና አገልግሎት እንደገለጸው እስራኤል በዛሬው እለት ጠዋት በቤይሩት ከተማ ደቡባዊ ዳርቻ እና ቾፊያት አካባቢ በሚገኘው የሬዲዮ ጣቢያ ላይ አራት ከፍተኛ ፍንዳታ ያስከተለ የአየር ጥቃት አድርሳለች።እስራኤል ሀማስ ጥቃት የከፈተበትን አንደኛ አመት ከሊባኖስ በሚተኮሱ ሮኬቶች ምክንያት የእንቅስቃሴ ገደብ በመጣሉ ውስን በሆነ መርሃግብር ታከብረዋለች። የእስራኤል ፕሬዝደንት ኢሳቅ ሄርዞግ የጥቃቱ አንደኛ አመት መታሰቢያ ከመድረሱ ከሁለት ቀናት በፊት “ቁስሉ” አልሻረም ብለዋል።ፕሬዝደንቱ አክለውም ኢራን እና አጋሮቿ በእስራኤል ላይ “ዘላቂ ስጋት” መደቀናቸውን ተናግረዋል።ፕሬዝደንቱ በመላው አለም ለሚገኙ አይሁዶች ባለስተላፉት መልእክት “በጥላቻ ታውረው እስራኤልን ለማጥፋት ቆርጠው ተነስተዋል” ያሏቸው ኢራን እና አጋሮቿ ቋሚ የሆነ ስጋት ደቅነዋል ብለዋል።የእስራኤል የጋዛ ዘመቻእስራኤል በትናንትናው እለት ነዋሪዎች በማዕከላዊ ጋዛ ከሚገኙት ኑሴራት እና ቡሬጂ ካምፖች ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላልፋለች። የእስራኤል የጦር ጄቶች በካምፖቹ ውስጥ በዘጠኝ ቦታዎች የሚገኙ ነዋሪዎች በፍጥነት እንዲወጡ እና ወደ ተከለሉት “ሰብአዊ ዞኖች” እንዲሄዱ የሚጠይቅ በራሪ ወረቀቶችን በትነዋል።እስራኤል ባለፈው አመት ጥቅምት ወር የደረሰባትን ያልተጠበቀ ጥቃት ተከትሎ በጋዛ በከፈተችው መጠነሰፊ የአየር እና የእግረኛ ጦር ጥቃት 41825 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የፍልስጤም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።ሀማስ በፈመጸው ጥቃት 1200 ሰዎችን የገደለ ሲሆን 1200 የሚሆኑትን ደግሞ አግቶ መውሰዱ ይታወሳል።እስራኤል በጋዛ ባደረገችው ዘመቻ መጠነሰፊ ውድመት ካደረሰች እና በርካታ የሀማስ መሪዎችን ከደገለች በኋላ ትኩረቷን በሊባኖስ ወደሚንቀሳቀሰው ሄዝባለ አድጋለች።
AL-AIN
More Stories
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን ጋር የሚያደርጉት ንግግር እየተመቻቸ መሆኑን ገለጹ።
የአሜሪካ ኮንግረስ በአለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ድምጽ ሰጠ
አስደንጋጩ የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት አልበረደም