የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰልጣኝ የበረራ አስተናጋጆችን በአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ተቀብለው አነጋግረዋል። አዛዡ በዚህ ወቅት ሀገርን ብሎም ተቋምን ለማገልገል በቅድሚያ የሀገር ፍቅር ስሜት ከአላማ ፅናት ጋር መላበስ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፤ የእርስ በእርስ መደጋገፍን እንደባህል መያዝ እንደሚገባ እና ከፋፋይ ከሆኑ ጎጂ አስተሳሰቦችም መራቅ ወሳኝ ነጥብ መሆኑንም ጠቁመዋል። የበረራ አስተናጋጆች ውስጣዊ አንድነታቸውን ይበልጥ በማጎልበት ከብሔርተኝነት ከሃይማኖት አክራሪነት እንዲሁም ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት ራሳቸውን ማራቅ እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል።
ተቋምን ብሎም ሀገርን ለማገልገል በቅድሚያ ጥብቅ በሆነ ሙያዊ ዲስፕሊን መታነፅ ያስፈልጋል – ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ

More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።