January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል የኢትዮጵያዊያን የአንድነትና የመከባበር ኃይል የሚያሳይ ትልቅ መሰባሰቢያ መድረክ ነው ሲሉ የበዓሉ ታዳሚዎች ገለጹ።

በበዓሉ ላይ ለመታደም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በባህላዊ አልባሳት አጊጠው አዲስ አበባ የተገኙ በርካታ ሰዎች በሆራ ፊንፊኔ በመሰባሰብ የኢሬቻ በዓልን እያከበሩ ነው።ከአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከአገር ውጪ የሚመጡ እንግዶች በጋራ ተሰባስበው የሚገናኙበት ታላቅ ሁነት መሆኑን የሚናገሩት የበዓሉ ታዳሚዎች፤ የኢሬቻ በዓል ሁሉም ያለውን ውበት አጉልቶ የሚያወጣበትና የሚያስተዋውቅበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ህብረተሰቡ ካለፉት ዓመታት ልምድ በመውሰድ የዘንድሮው በዓል ድባቡ የተለየና ያማረ እንዲሆን ማድረጉንም ነው የጠቀሱት፡፡ በተለይም በዓሉ እሴቱን ጠብቆ ከልጅ እስከ አዋቂ በመልካም ስነ-ምግባር በዓሉን እያከበሩ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡የአዲስ አበባ ነዋሪዎችና የፀጥታ አካላት ያዳረጉት አቀባበል ማራኪ መሆኑን በመመስከር ለተደረገላቸው ሁሉ ማመስገናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።የዘንድሮው የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ”ኢሬቻ ለባህላችን ሕዳሴ” በሚል መሪ ሃሳብ በኅብረ ቀለማት ባሸበረቀ መልኩ በመከበር ላይ ይገኛል።