January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የ ‘ሆረ ፊንፊኔ’ ኢሬቻ በዓል በድምቀት እንዲከበር ያደረጉ አካላትን አመሰገኑ

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የ ‘ሆረ ፊንፊኔ’ ኢሬቻ በዓል በድምቀት እንዲከበር አስተዋጽዖ ያደረጉ አካላትን አመሰገኑ፡፡የ ‘ሆረ ፊንፊኔ’ ኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ በድምቀት ተከብሯል፡፡ይህን ተከትሎም በዓሉን እሴቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር ያደረጉ አካላትን ማመስገናቸውን የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡በነገው ዕለትም በቢሾፍቱ ከተማ ‘ሆረ ሀርሰዲ’ እንደሚከበር ገልጸው÷ በዓሉ ዕሴቱን በጠበቀ ሁኔታ በድምቀት እንዲከበር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅረበዋል፡፡

EBC