October 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የወባ በሽታን ለመከላከል በሚደረጉት ጥረቶች ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የበኩላቸውን ድረሻ መወጣት እንዳሉባቸው የየኪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አስታወቀ።

በተለይም በሽታው ለመከላከል የትንኝ መራቢያ ቦታዎችን ማፋሰስና ማዳፈን ስራ ላይ ህብረተሰቡ ትኩረት አደርገው እንድሰራ ጽ/ቤቱ አሳስቧል።የኪ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተካልኝ ባሳ እንደገለጹት ለህብረተሰቡ ዋነኛ የጤና ስጋት የሆነውን የወባ በሽታን ለመከላከል የአካባቢ ንጽህና በመጠበቅ ዙሪያ ሰፊ ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።እንደ ወረዳ ከ22ቱ ቀበሌዎች 14 የወባ መቀነት ተብሎ በተለዩት አካባቢዎች ግብረ -ኃይ ተቋቁመው ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።ወቅቱ ቡና የሚሰበሰብበት በመሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ጊዜያዊ ከአካባቢው ርቀው ስለሚቆዩ በተለይ ሴቶችና ህጻናት ለበሽታው ስለሚጋለጡ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ኃላፊ ተናግረዋል። የአጎበር አጠቃቀምን በትክክል ተግባራዊ ማድረግ ከህብረተሰቡ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል። ዘጋቢ ታዲዮስ ግርማ