በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስል ጄነራል ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ÷ በሊባኖስ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ዜጎች ከሊባኖስ መውጣት የሚችሉበትን መንገድ እያመቻቸ መሆኑን አስታውቋል፡፡በዚሁ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የሚፈልጉ እና እስከ አሁን ያልተመዘገቡ ወገኖች አስፈላጊውን መረጃ በማዘጋጀት እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡ለምዝገባ አስፈላጊ የሆኑት መረጃዎችም÷ ሙሉ ስም ከነአያት(ፓስፓርት ላይ እንደተፃፈው)፣ የፓስፖርት ቁጥር፣ በሊባኖስ የቆይታ ጊዜ፣ የሊባኖስ ስልክ ቁጥር መሆናቸውን ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡ለምዝገባ የተዘጋጁት ስልክ ቁጥሮችም÷ 03-29-89-78፣ 76-03-08-23፣ 81-99-46-34፣ 70-29-80-91፣ 81-80-25-18፣ 70-84-25-24 እና 81-09-27-46 መሆናቸውን የጽሕፈት ቤቱ መረጃ አመላክቷል፡፡ጽሕፈት ቤቱ ቀደም ሲያል ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ የተመዘገቡና መመዝገባቸውን ያረጋገጡ ወገኖች በድጋሚ እንዳይመዘገቡ አሳስቧል፡፡
Woreda to World
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።