January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የሸካቾ ዘመን መለወጫ/ማሽቃሮ/ በዓል በደማቅ ባህላዊና ታሪካዊ ስነስርዓቶች “በሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ ገጫ” በድምቀት ተከብሮ ውሏል።

የሸካቾ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ማሽቃሬ ባሮ” በክልሉ ከሚገኙ ቱባ ባህሎች አንዱ መሆኑንና የህዝቦችን ትስስር ፣አንድነት፣ ህብረብሔራዊነትን በማጎልበት ረገድ ባህል ትልቅ ፋይዳ እንዳለው የክልሉ ባህል ቱርዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ተናገሩ ።ባህልን ማልማት፣መንከባከብ ፣መጠበቅ፣ የህዝቦች ትልቅ የማዕዘን ድንጋይ፣መነሻ ታሪካቸውን የሚያዩበት መነጽር፣ ዘላቂ ልማትና ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያስችል ወሳኝ እሴት ነው ሲሉም የቢሮው ኃላፍ አክለዋል።የባህልና የቋንቋ መብቶች ተጠብቀው የሚካሄዱት ክዋኔዎች ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅሙ ከፍተኛ ስለሆነ ለትውልድ ማስተማርና ማስተላለፍ ያስፈልጋል ተብሏል።