በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተጀመረውን የኮሪደር ልማት ስራ አጠናክሮ ለማስቀጠል የተቀናጀ ርብርብ እንደሚያስፈልግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ የኮሪደር ልማት ስራን በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ከተሞች ተግባራዊ ማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮችና የዝግጅት ሂደት ላይ ያተኮረ ውይይት በአርባምንጭ ከተማ እያካሄዱ ነው። አቶ ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት፣ ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ምቹና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የኮሪደር ልማት ስራን አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል። የተሻለ ከተማ ለቀጣይ ትውልድ ለማስረከብ እየተደረገ ላለው ሂደት የኮሪደር ልማት ስራ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ጠቅሰው፤ ለዚህም የከተማ ነዋሪዎችና የስራ አመራሩ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። በውይይቱ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት እየተሰተፉ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
Woreda to World
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።