ይህ ሜጋ ፕሮጀክት የመንግሥታችን በፍጥነት፣ በግዝፈት እና በንፅህና የመገንባት ጽኑ አቋማችን የማሳያ ነው። እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን በፍጥነት እና በብቃት አጠናቅቆ ዝግጁ የማድረግ ተምሳሌትም ነው። ይህ በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገራችን ያሉ ተመሳሳይ ፋብሪካዎች ተደምረው የሚያመርቱትን ሃምሳ ከመቶ የሚያመርት ፋብሪካ እውን እንዲሆን የተሳተፋችሁ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ።ከሁለት አመታት በኋላ ወደዚህ ስፍራ ስመለስ የአመራር መርሆዎቻችን ማሳያ በሆነው በሥራው ፍጥነት ተደንቄያለሁ። ፕሮጀክቱ በመሰል ጠንካራ ሥራ መጪው ትውልድ ድህነትን እንደማይወርስ ይልቁንም ለእድገት እና ብልጽግና ጥሩ መደላድል እንደሚጠብቀው ያሳያል።እንደ ለሚ ያሉትን የኢንደስትሪ ፕሮጀክቶች በመላው ሀገራችን ካባዛን በሥራ ፈጠራ እና በሀገራዊ እድገት ላይ የሚኖረው የመባዛት ፍሬ አቻ የማይገኝለት ይሆናል። በተለይም በብረት ምርት፣ በማዳበሪያ ምርት ብሎም በሰፊው የኢንደስትሪ እና ግብርና ልማት አብዮት የሚኖረው ተፅዕኖ ሰፊ ነው።እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ትልቅ ሀገራትን የሚገዳደሩ ፈተናዎች ከፍ ያለ ደረጃ ያላቸው መፍትሔዎችን ይሻሉ። በመንግሥት እና የግሉ ዘርፍ የሚኖር የጋራ ትብብር እምቅ ሀብትና እድሎችን ለመጠቀም ብሎም ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት ቁልፍ ነው። በመሰል ሥራዎች ላይ ኢንቬስት በማድረግ የብዙ ዜጎችን ሕይወት ማሻሻል እንዲሁም ክብር ያለው አኗኗር እንዲኖሩ ማድረግ ይቻላል።”ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Woreda to World
More Stories
የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ
የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እለት በርካታ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈችፒዮንግያንግ በጥቂቱ ሰባት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሷን የጃፓን የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል