በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተመድ ጉባዔ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከዴንማርክ አቻቸው ላርስ ሎክ ራስምሰን ጋር ተወያይተዋል። አምባሳደር ታዬ በውይይቱ ላይ ዴንማርክ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት አባል ሆና በመመረጧ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ፤ በወቅታዊ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች እና ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ ባላት ቁርጠኝነት ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል። በተያያዘ አምባሳደር ታዬ ከተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሼህ ሻክቡት ናህያን አል ናህያን ጋር በሁለትዮሽ እና በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኀንነት ዙሪያ መክረዋል። ሶማሊያን በተመለከተ ባደረጉት ውይይት አምባሳደር ታዬ የቀጣናው አገራት ዋጋ የከፈሉበት እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከፍተኛ ወጪ ያወጣበት የሶማሊያ ደህንነት እንዲቀጥል ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ከድህረ አትሚስ በኋላ የሚኖረው የኃይል ሥምሪት ጊዜ ተወስዶ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከዴንማርክ አቻቸው እና ከተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያዩ

More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።