January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከኡጋንዳ እና ርዋንዳ አቻቸው ጋር ተወያዩ

በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (የተመድ) ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከኡጋንዳ እና ርዋንዳ አቻቸው ጋር ተወያይተዋል።አምባሳደር ታዬ ከኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሊቪየር ኑሁንጊሬሄ እና የርዋንዳ ውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ጄጄ ኦዶንጎ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።ከርዋንዳው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄጄ ኦዶንጋ ጋር በነበራቸው ውይይት በናይል የውሃ ሃብት ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ ሁለቱ ሀገራት ስላላቸው የጋራ አቋም ዙሪያ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።ከኡጋንዳው አቻቸው ጋር በነበራቸው ውይይትም በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የሰላም ሁኔታ ላይ የመከሩ ሲሆን፤ በድህረ በሶማሊያ ከአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ሰላም ማስከበር ተልዕኮ (አትሚስ) መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች እና አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።ኢትዮጵያና ኡጋንዳ በሶማሊያ ሰራዊት አሰማርተው የነበሩ በመሆናቸው ድህረ አትሚስ ሽብርተኝነትን በመዋጋት የተመዘገበው ውጤት ወደኋላ በማይመልስ መልኩ መፈጸም እንዳለበት መክረዋል።በጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ ኡጋንዳ የምታስተናግደው የናይል ጉባዔ የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ወደ ተግባር እንዲገባ የሚያስችሉ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት እንደሚሆን ያላቸውን እምነት አምባሳደር ታዬ ገልጸዋል።

FBC