በተለያየ ከተማ ይኖራሉ የተባሉት ሴቶቹ ከብራድፒት ጋር ጥሩ የፍቅር ጊዜ እንደሚያሳልፉ ቃል ገብቶላቸው ነበርብራድፒት ነኝ በሚል ሁለት ሴቶችን 362 ሺህ ዶላር ያጭበረበረው ሰውበታዋቂው አሜሪካዊ የሆሊውድ አክተር በሆነው ብራድ ፒት አድናቂዎች ስም የተከፈተ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ለእንስቶቹ መጭበርበር መነሻ ሆኗል፡፡በስፔን የተለያዩ ከተሞች ይኖሩ የነበሩ ሁለት ሴቶች ደግሞ በዚሁ የትስስር ገጽ ላይ እውነተኛው ብራድፒት አልፎ አልፎ መልዕክት ያጋራ ነበርም ተብሏል፡፡ይህንን የማህበራዊ ትስስር ገጽ ይከተሉ የነበሩት እነዚህ ሁለት ሴቶች ብራድፒት ነኝ የሚል ሰው መልዕክት ልክላቸዋል፡፡ቀስ በቀስ በግል ስልክ ቁጥራቸው እና ኢሜይል አድራሻቸው አማካኝነት ማውራታቸውን የቀጠሉት ሴቶቹ በመጨረሻም ግንኙነቱ ወደ ፍቅር እንዳደገም ተገልጿል፡፡ከብራድፒት ጋር እያወሩ መሆናቸውን ያመኑት እነዚህ ሴቶችም ንግድ ማስፋታት እንደሚፈልግም ነግራቸዋል፡፡የፍቅር ግንኙነት እንደሚጀምሩ እርግጠኛ የሆኑት እነዚህ ሴቶችም ገንዘብ ላኩልኝ ሲላቸው እንደላኩለት ለፖሊስ ተናግረዋል፡፡እየሱስ ነኝ በሚል 300 ሺህ ዩሮ የተቀበለው አጭበርባሪ ተያዘአንዷ ሴት ብቻ 195 ሺህ ዶላር ብራድ ፒት ነኝ ለሚለው ሰው የላከች ሲሆን ሌላኛዋ ሴትም 167 ሺህ ዶላር በድምሩ 362 ሺህ ዶላር ተታለው መላካቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡ገንዘባቸው መበላቱን እና እናሳልፋለን ያሉት ፍቅር የውሸት መሆኑን የተረዱት እነዚህ ሴቶችም ጉዳዩን ይዘው ወደ ፖሊስ ያመራሉ፡፡ፖሊስ ባደረገው ማጣራትም አጭበርባሪዎች ሰዎችን እያታለሉ ገንዘብ እየመዘበሩ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን አምስት ተጠርጣሪዎችን እንደያዘ አስታወቋል፡፡እንዲሁም ፖሊስ ባደረገው ክትትል 84 ሺህ ዶላር ከአጭበርባሪዎቹ ላይ ማስመለሱንም አስታውቋል፡፡ተጨማሪ ተጠርጣሪዎች እየተፈለጉ ነው የተባለ ሲሆን አጭበርባሪዎች ሐሰተኛ ማንነት እና መረጃዎችን እየተጠቀሙ መሆናቸው ጉዳዩን በቀላሉ መቆጣጠር እንዳይቻል ፈተና ሆኗል ተብሏል፡፡
AL-AIN
More Stories
ዶናልድ ትራምፕ 47ኛ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ
ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እለት በርካታ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈችፒዮንግያንግ በጥቂቱ ሰባት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሷን የጃፓን የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል
የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት እና የደረሱ ውድመቶች በንጽጽር